Fana: At a Speed of Life!

የሃላል ምግብ እና ቱሪዝም አውደ ርዕይ እና ጉባኤ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 2 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የከዒድ እስከ ዒድ የማጠናቀቂያ መርሐ ግብር አካል የሆነው የሃላል ምግብ እና ቱሪዝም አውደ ርዕይ እና ጉባኤ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።
የሃላል ኢንዱስትሪ በዓለም አቀፍ ገበያ በቢሊየን የሚቆጠር ዶላርን የሚያንቀሳቅስና ሀገራት የወጪ ንግድ ገበያቸውን የሚያስፋፉበት አማራጭ መሆኑ በመክፈቻ መርሐ ግብሩ ላይ ተገልጿል።
አውደ ርዕዩ ኢትዮጵያ በቱሪዝም እና በወጪ ንግድ ዘርፍ ያላትን አማራጭ ሃብት ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እንድታስተዋውቅ ማስቻል ያለመ መሆኑ ተመላክቷል፡፡
የሃላል ምግብ እና ቱሪዝም አውደ ርዕይ እና ጉባኤ ለቀጣይ ሶስት ቀናት እንደሚቆይም ተጠቁሟል፡፡
በቆንጂት ዘውዴ
 
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
 
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.