Fana: At a Speed of Life!

ኢኮኖሚው የሚያመነጨውን ገቢ በአግባቡ ለመሰብሰብ ዘርፉን በእውቀትና በቁርጠኝነት መምራት ይገባል -አቶ አወል አርባ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 2 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢኮኖሚው የሚያመነጨውን ገቢ በአግባቡ ለመሰብሰብ በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች ዘርፉን በእውቀትና በቁርጠኝነት መምራት እንደሚገባቸው የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባ ገለጹ።
በክልሉ በ2014 የገቢ አሰባሰብ እቅድ አፈጻጸምና የ2015 በጀት ዓመት እቅድ በተመለከተ ከወረዳ አመራሮች ጋር በሰመራ ከተማ ምክክር ተካሂዷል።
የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባ በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት÷ በክልሉ ኢኮኖሚው የሚያመነጫቸው የተለያዩ የገቢ አማራጮች አሉ፤ይሁንና እስካሁን በክልሉ እየተሰበሰበ ያለው ገቢ በዋናነት ከስራ ግብርና ከጨው ምርት እንዲሁም ከሚታወቁ የገቢ አርዕስቶች እንደሆነ ተናግረዋል።
በተለይም የህብረተሰቡ የኢኮኖሚ መሠረት ከሆነው የቁም እንስሳትና የመሬት መጠቀሚያ ግብርን ጨምሮ የማዘጋጃ ቤትና ተያያዥ የገቢ አማራጮች ላይ ትኩረት በመስጠት መሰብሰብ እንደሚገባ አመልክተዋል።
ለተግባራዊነቱም በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች ዘርፉን በእውቀትና በቁርጠኝነት ከፊት ሆኖ መምራት ተቀዳሚ ተልዕኳቸው አድርገው መውሰድ እንደሚገባቸው ማስገንዘባቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.