Fana: At a Speed of Life!

የሲሚንቶ ሽያጭ በአዲስ መልክ እንደሚጀመር የሲዳማ ክልል ንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሕገወጥ የሲሚንቶ ንግድን ለመቆጣጠር በአዲስ መልክ ሽያጭ እንደሚጀመር የሲዳማ ክልል ንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ አስታወቀ፡፡
የቢሮው ኃላፊ አቶ አሻግሬ ጀንበሬ በሰጡት መግለጫ÷ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ያወጣውን መመሪያ መሠረት በማድረግ ክልሉን ታሳቢ ባደረገ መልኩ አዲስ መመሪያ መውጣቱን ጠቅሰው÷ ከዚህ በፊት በሲሚንቶ አከፋፋዮችና ቸርቻሪ ነጋዴዎች ላልተወሰነ ጊዜ ሽያጭ እንደማይቀጥሉ አስታውቀዋል።
እየታየ ያለውን የሲሚንቶ ምርት አቅርቦት እጥረት ለመቅረፍ በሲዳማ ዴቨሎፕመንት ኮርፖሬሽን እና አስ ኤም ሀኃከላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ አማካይነት እንደሚቀርብ እና ምርቱንም በ44 የወጣት ማኅበራት በኩል እንደሚሠራጭ አመላክተዋል፡፡
 
በዚህኛው ዙር ብቻም÷በሐዋሳ፣ ለኩ፣ አለታ ወንዶ እና በዳዬ ከተሞች አከፋፋዮች በኩል የሲሚንቶ ሥርጭት እንደሚካሄድ የቢሮው መረጃ አመላክቷል፡፡
 
የግንባታ ሂደቶችን ለመቆጣጠር ሥልጣን የተሰጠው የክልሉ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ሲሚንቶ እንደሚያስፈልጋቸው ለሚያቀርባቸው÷ የመንግሥት ፕሮጀክቶች (የትምህርት፣ ጤና፣ ውኃ እና ሌሎችም) ቅድሚያ እንደሚሰጥ ጠቁመው÷ ለግል አልሚዎች እና ለኅብረት ሥራ ማኅበራት አገልግሎቱ እንደሚቀርብ ተናግረዋል፡፡
 
የሲሚንቶ ድጋፍ የሚሰጡ አካላት ለትኛውም አገልግሎት ተጨማሪ ክፍያ ሳይጠይቁ ለህብረተሰቡ የተቀላጠፈ አገልግሎት እንዲሰጡና የሲሚንቶ አከፋፋዮችም መንግሥት ባወጣው ዋጋ ብቻ እንዲሸጡና የተፈቀደለትን ሲሚንቶ ይዞ የሚቀሳቀስ አካል ሕጋዊ ደረሰኝ እንዲይዝ የቢሮ ኃላፊው አሳስበዋል፡፡
 
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.