Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ ከ831 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነቡ ፕሮጀክቶች ተመረቁ

 

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከ831 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው ከ100 በላይ ፕሮጀክቶችን ለአገልግሎት ክፍት አድርጓል፡፡

የከተማ አስተዳደሩ የከተማውን የፀጥታ ችግሮች ለመቅረፍ ከ320 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የገነባቸው ሶስት የተለያዩ ዘመናዊ የፖሊስ መምሪያ ህንፃዎችና ከ511 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸውን ከ100 በላይ ፕሮጀክቶች በዛሬው ዕለት አስመርቋል፡፡

በምረቃ መርሐ ግብሩ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ፣ ምክትል ከንቲባ አቶ ጃንጥራር አባይ ፣ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ጥራቱ በየነ፣ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽነር ጌቱ አርጋውን ጨምሮ ሌሎች የከተማው የካቢኔ አባላት እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችተገኝተዋል፡፡

ከንቲባ አዳነች ÷ ኢትዮጵያን የማደናቀፍ እቅድ የያዙ ሃይሎች ብዙ እኩይ ተግባር በሚያካሂዱበት በዚህ ሰዓት ቃላችንን ጠብቀን በርካታ ፕሮጀክቶችን መርቀን ለአገልግሎት ክፍት ማድረግ በመቻላችን እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል፡፡

ከተማችን አዲስ አበባ የሀገራችን ዋና ከተማ ፣ዓለም አቀፍ ሦስተኛ የዲፕሎማሲ ማዕከልና የአፍሪካ ሕብረት መቀመጫ እንደመሆኗ የፖሊሳዊ አገልግሎት ተደራሽነትን ወቅቱ በሚጠይቀው ልክ በማሳደግ ለልማታችን በሚሆን መልኩ የከተማችንን ሁለንተናዊ ሰላም ማረጋገጥ ያስፈልጋል ነው ያሉት፡፡

የአዲስ አበባ ፖሊስ አባላት ራሳቸውን ለህዝብ ሰጥተው እና የእውነት ቃል ኪዳናቸውን ጠብቀው በሰብዓዊነት ማገልገል በሚለው መርሕ ህዝብን ማገልገላቸውን እንዲቀጥሉ አሳስበዋል፡፡

የከተማ አስተዳደሩ ፖሊስን ለማጠናከር ማንኛውንም አይነት ድጋፍ በማድረግ በኩል የሚሰስተው ነገር እንደሌለም ከንቲባ አዳነች ገልፀዋል፡፡

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ጌቱ አርጋው በበኩላቸው ባለፉት ጊዜያት የከተማው ፖሊስ ከህብረተሰቡ ጋር ባደረገው ብርቱ ጥረት ወንጀልን በመቀነስ በኩል አበረታች ለውጥ መታየቱን ገልፀዋል፡፡

በተለይም የፀረ ሰላም ሃይሎችን ሴራ በማክሸፍ በከተማዋ አስተማማኝ ሰላም ማስፈን ተችሏል ነው ያሉት፡፡

የከተማ አስተዳደሩም ፖሊስን ለማጠናከር እያደረገ ያለውን ጥረት አድንቀው÷ አሁንም የከተማ አስተዳደሩ በሁሉም ክፍለ ከተሞች ተመሳሳይ የፖሊስ ተቋማትን እንደሚያስገነባ ገመናገራቸውን ከከንቲባ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.