Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያውያንን ያጋመዱ የአብሮነት እሴቶች በትምህርት ስርዓት ውስጥ ቦታ አጥተው መቆየታቸው እንዲሸረሸሩ አድርጓል – ምሁራን

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያውያንን ያጋመዱ የአብሮነት እሴቶች በትምህርት ስርዓት ውስጥ ቦታ አጥተው መቆየታቸው እንዲሸረሸሩ ማድረጉን የማህበራዊ ሳይንስ ባለሙያዎች ተናገሩ።

የማህበራዊ ሳይንስ እና የፍልስፍና ተመራማሪው ዶክተር ተሾመ አበራ ፥ ማህበራዊ እሴቶቻችን የተሸረሸሩት በትምህርትና በፖለቲካ ስርዓት መሆኑን ገልጸዋል።

የጅማ ዩኒቨርሲቲ የማህበራዊ ሳይንስ መምህሩና ተመራማሪ ነጋ ጅባት ፥ በስርዓተ ትምህርቱ ሀገር በቀል እውቀቶች አለመካተታቸውን እንደ አንድ ችግር ይጠቅሱታል።

ባለሙያዎቹ ትምህርት ስርዓቱ አብሮነት የሚያጎሉና የሚያጎለብቱ እሴቶችን ማካተት እንዳለበት መክረዋል።

የሃይማኖት ተቋማት የሚያስተምሩትን በተግባር ማሳየት እሴቱ እንዲጠበቅ ያደርጋል ብለዋል።

የማህበራዊ ሳይንስ ባለሙያዎቹ አያይዘውም፥ የአብሮነት እሴቶች ለማስቀጠልና ለማቆየት ባህላዊ ተቋማት ሚናቸው የጎላ እንደሆነ አንስተዋል፡፡

በአልማዝ መኮንን

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.