Fana: At a Speed of Life!

ፊንላንድ እና ስዊድን ኔቶን እንዲቀላቀሉ ከአሜሪካ ይሁንታ አገኙ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ፊንላንድ እና ስዊድን የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (ኔቶ) እንዲቀላቀሉ በሚያስችሉት ፕሮቶኮሎች ላይ መፈረማቸው ተገለጸ፡፡

ሀገራቱ የቃል ኪዳን ድርጅቱን እንዲቀላቀሉ ከዴሞክራቲክ እና ከሪፐብሊካን ሴናተሮች ጠናካራ የይሁንታ ድጋፍ እንደተቸራቸው ሲ ጂ ቲ ኤን ዘግቧል፡፡

የሀገራቱ ዘመናዊ የመከላከያ ኃይል በቀጣይ ከኔቶ ጋር በቅርበት እንደሚሰራም ታምኖበታል ተብሏል፡፡

ባለፈው ወር ሠላሳ የኔቶ አጋር ሀገራት ስዊድን እና ፊንላንድ የቃል ኪዳን ድርጅቱን እንዲቀላቀሉ የሚያስችላቸውን ፕሮቶኮል መፈረማቸው ይታወሳል።

የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (ኔቶ) በፈረንጆቹ ሚያዝያ 4 ቀን 1949 በአሜሪካ የተመሰረተ እና ኒውክሌር የታጠቀ እጅግ ጠንካራ ኅብረት እንደሆነ ይነገርለታል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.