Fana: At a Speed of Life!

ከ176 ሺህ በላይ የክስ መዛግብት ዕልባት አገኙ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2014 በጀት ዓመት በፌዴራል ፍርድ ቤቶች ከ176 ሺህ በላይ መዛግብት ዕልባት ማግኘታቸውን ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ አስታወቀ።
የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት መዓዛ አሸናፊ በፌዴራል ፍርድ ቤቶች እና በፌደራል ዳኞች አስተዳደር ጉባዔ በ2014 በጀት ዓመት የተከናወኑ ተግባራትንና የ2015 የትኩረት አቅጣጫዎችን አስመልክቶ ዛሬ መግለጫ ሰጥተዋል።
ፕሬዝዳንቷ በመግጫቸው በዳኝነት ነጻነት፣ በአገልግሎት ቅልጥፍና፣ በዳኝነት ተጠያቂነትና ሌሎች በዳኝነት ሥርዓቱ የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራትና ውጤቶችን ገልጸዋል።
በዚህም በ2014 በጀት ዓመት በአጠቃለይ በፌደራል ፍርድ ቤቶች 176 ሺህ 797 መዛግብት ዕልባት ማግኘታቸውን ገልጸዋል።
ይህም ከ2013 በጀት ዓመት የመዛግብት አፈጻጸም ጋር ሲነጻጸር፥ ከ5 ሺህ 500 መዛግብት በላይ ብልጫ አለው ማለታቸውን የኢዜአ ዘገባ ያመላክታል።
ፍርድ ቤቶች መዛግብትን የሚመረምሩት እና እልባት የሚሰጡት የፍርድ ቤቶች ፕሬዝዳንቶችን ጨምሮ በ392 ዳኞች አማካይነት መሆኑን ጠቁመው፥ የዳኛና መዛግብት ጥምርታ 1ዳኛ ለ451 መዛግብት መሆኑን አንስተው አሁንም ጫና መኖሩን አስረድተዋል።
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.