Fana: At a Speed of Life!

በጋምቤላ የፀጥታ ችግሮችን ለመፍታት ውይይት እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጋምቤላ ክልል የፀጥታ ምክር ቤት በክልሉ የሚስተዋሉ የፀጥታና የሰላም ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት በሚያስችል ሁኔታ ላይ ውይይት እያካሄደ መሆኑ ተገለጸ፡፡

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ ÷ በክልሉ የፀጥታ ምክር ቤት አደረጃጀት እና የበታች የፀጥታ ምክር ቤቶችን በሚገባ ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ውይይት እየተካሄደ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡

በውይይቱ እስካሁን የተከናወኑ ዋና ዋና የፀጥታ ስራዎችን በመገምገም ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች እና ውሳኔዎች ይቀመጣሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ከጋምቤላ ክልል የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.