Fana: At a Speed of Life!

የሶማሌ ክልል ምሁራን የድርሻቸውን እንዲወጡ ተጠየቁ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሀመድ የሶማሌ ክልል ምሁራን የድርሻቸውን እንዲወጡ ጠየቁ፡፡
አቶ ሙስጠፌ መሀመድ ምሁራን በወቅታዊ የጸጥታ ሁኔታ ላይ በሚኖራቸው ሚና እና ከሀገራዊ ነባራዊ ሁኔታ ጋር ያለውን እውነታ ግንዛቤ ለማስጨበጥ ያለመ ውይይት አካሂደዋል፡፡
በውይይታቸውም ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ የክልሉ ምሁራን የድርሻቸውን እንዲወጡ ጠይቀዋል፡፡
የክልሉ ምሁራን በበኩላቸው÷ ከሀገሪቱና ከክልሉ የጸጥታ አካላት ጋር በቅንጅት ለመስራትና የራሳቸውን ድርሻ ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል፡፡
ምሁራኑ ከሕዝቡ ጋር በመተባበር የክልሉን ብሎም የሀገሪቱ ሰላምና መረጋጋት ለማደፍረስ የሚሞክር ማንኛውንም ፀረ ሰላም ኃይል ለመመከት ዝግጁ መሆናቸውን የብልፅግና ፓርቲ መረጃ አመላክቷል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.