Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ ለሚገኙ ሆስፒታሎችና ጤና ጣቢያዎች 31 አምቡላንሶች ተከፋፈሉ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 5 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ በከተማው ለሚገኙ ሆስፒታሎችና ጤና ጣቢያዎች 31 አምቡላንሶችን አከፋፈለ።

የጤና ቢሮው ኃላፊ ዶክተር ዮሐንስ ጫላ እንደገለፁት፥ አምቡላንሶቹ የድንገተኛ አደጋን ጨምሮ የእናቶችና የህፃናትን ህክምና አገልግሎት በዘመናዊ መንገድ ለመስጠት የሚያግዙ ናቸው።

ከአምቡላንሶቹ ውስጥ 25ቱ ለጤና ጣቢያዎች እና ስድስቱ ደግሞ ለሆስፒታሎች ተከፋፍለዋል።

የሆስፒታሎች እና ጤና ጣቢያ ተወካዮችም የአምቡላንሶችን ቁልፍ ተረክበዋል።

በዘመን በየነ

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.