Fana: At a Speed of Life!

ዶናልድ ትራምፕ ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አወጁ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 5 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከኮሮና ቫይረስ ስርጭት ጋር በተያያዘ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አወጁ።

ፕሬዚዳንቱ የቫይረሱን ስርጭት ለመቆጣጠር የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ በሚል ነው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ያወጁት።

ትራምፕ ባደረጉት ንግግር ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ ለአሜሪካ ቀጣዮቹ 8 ሳምንታት ወሳኝ መሆናቸውን ገልጸዋል።

ፕሬዚዳንቱ ከትናንት እኩለ ሌሊት ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ የጉዞ እገዳ በአውሮፓ ሃገራት ላይ መጣላቸው ይታወሳል።

እገዳው የአውሮፓ ሃገራት ዜጎች ወደ አሜሪካ እንዳይገቡ የሚከለክል ሲሆን፥ በአውሮፓ የሚገኙ አሜሪካውያንን ግን አያካትትም።

ከዚህ ባለፈም እንግሊዝ ላይ ይህ እገዳ ተግባራዊ እንደማይሆንም መግለጻቸው የሚታወስ ነው።

የኮሮና ቫይረስ ዓለም ላይ ከ138 ሺህ በላይ ሰዎችን ሲያጠቃ ከ5 ሺህ በላይ ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ሳቢያ ለህልፈት ተዳርገዋል።

ቫይረሱ በርካታ ሃገራትን እያዳረሰ ሲሆን፥ የዓለም ጤና ድርጅትም “አውሮፓ የቫይረሱ ማዕከል” መሆኗን ገልጿል።

ከቫይረሱ ጋር በተያያዘ አሜሪካን ጨምሮ በበርካታ ሃገራት የአክሲዮን ገበያ ከፍተኛ ቅናሽ አሳይቷል።

ምንጭ፦ ሬውተርስ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.