Fana: At a Speed of Life!

አቶ ሽመልስ አብዲሳ በኦሮሚያ ክልል ለተመዘገበው የአረንጓዴ አሻራ ስኬት ምስጋና አቀረቡ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 8 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ በክልሉ ለተመዘገበው የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ስኬት ምስጋና አቀረቡ።
በኦሮሚያ ክልል በዚህ አመት ለመትከል ከታቀደው 4 ነጥብ 35 ቢሊየን ችግኝ ውስጥ 4 ነጥብ 39 ቢሊየን ችግኝ መትከል ተችሏል።
ርዕሰ መስተዳድሩም ለታየው የላቀ አፈጻጸም ህብረተሰቡ ላደረገው ተሳትፎ ምስጋና አቅርበዋል።
ባስተላለፉት መልዕክትም “በህዝባችን ተሳትፎ የተገኘው ድል የእቅዳችንን ትክክለኛነት ያረጋገጠ ነው” ብለዋል።
የተተከሉ ችግኞችን መንከባከብ፣ የተፋሰስ ልማት ስራውን ማስቀጠል እና በቀጣይ አመት የሚተከሉ ችግኞችን ማዘጋጀት እንደሚገባም አስገንዝበዋል።
“በህዝባችን አንድነትና ሁለንተናዊ ተሳትፎ የድህነት ተራራዎችን ሰብረን ሁለንተናዊ ብልፅግናን የምናረጋግጥበት ጊዜ ሩቅ አይደለም” ብለዋል በመልዕክታቸው።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.