Fana: At a Speed of Life!

አካባቢያዊ ምርጫን ማከናወን የሚያስችል ውይይት እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 9 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አካባቢያዊ ምርጫን ለማከናወን የሚያስችለውን ውይይት ከባለድርሻ አካላት ጋር እያደረገ ነው ።

በኢትዮጵያ ለአምስተኛ ጊዜ በሚደረገው አካባቢያዊ ምርጫ ለሚደረገው ዝግጅት ቦርዱ ያስጠናውን ጥናት ተከትሎ ነው የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች እና ሌሎችም 160 የሚሆኑ ባለድርሻ አካላት ተሳታፊ የሆኑበት ውይይት እየተካሄደ ያለው።

የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ አካባቢያዊ ምርጫ አስፈላጊቱ እጅግ ጉልህ መሆኑን ተናግረዋል።

አካባቢያዊ ምርጫን ለማከናወን እና ትክክለኛ ልምምድን ከአዳጊ ሀገራት ለመማር ውይይቱ መዘጋጀቱን ገልጸዋል።

ምርጫውን በየክልሎቹ ለማስፈፀም ፣ የሚገጥሙ ችግሮች እና ሊኖሩ የሚችሉ የህግ ማሻሻያዎች ለውይይቱ ግብዓት እንዲሆኑ መድረኩ መዘጋጀቱንም ጠቅሰዋል።

በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚደረገው አካባቢያዊ ምርጫ ከቀበሌ ጀምሮ እስከ ወረዳ እና ዞን ድረስ ዜጎች ተወካዮቻቸውን በመምረጥ ዴሞክራሲያዊ ስርዓትን የሚያዳብሩበት ነው ብለዋል።

በአካባቢያዊ ምርጫ እና አካባቢያዊ የመንግስት አስተዳደርን በተመለከተም ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፌደራሊዝም ጥናት ማዕከል ጥናት በዶክተር ዘመላክ አየለ ቀርቧል።

በዚህ ወቅትም አካባያዊ ምርጫ ውክልናን ለማስፋት እና በፖለቲካ ሂደት ውስጥ ምህዳሩን ለማስፋት እና ውድድርን ለመፍጠር በከፍተኛ ደረጃ እንደሚረዳ የሀገራትን ተሞክሮ በማቅረብ አስረድተዋል።

በፀጋዬ ወንድወሰን

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.