Fana: At a Speed of Life!

የከፍተኛ ትምህርት የመውጫ ፈተና ማስፈጸሚያ መመሪያ ጸደቀ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የከፍተኛ ትምህርት አገራዊ ቅድመ ምረቃ የመውጫ ፈተናን በአግባቡ ለመምራትና ለማስተዳደር የተዘጋጀው የፈተና ማስፈጸሚያ መመሪያ ጸደቀ።

የትምህርት ሚኒስቴር እንዳስታወቀው÷ መመሪያው በመውጫ ፈተና ዝግጅት ሊካተቱ ስለሚገባቸው ሀገራዊ ዝቅተኛ የትምህርት ብቃት መመዘኛዎችን ፣ የሙያ ሥነምግባር ደምቦችን እና ተቋማት ሊከተሏቸው የሚገቡ የአሠራር ስነ- ስርዓቶችን አካቷል ።

መመሪያው የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅና ሀገሪቱ የምትፈልገውን የሠለጠነ የሠው ሃይል ለማፍራት ከሚደረጉ ማስፈፀሚያ ስልቶች አንዱ ነው ተብሏል።

በመመሪያው ዝግጅት ሂደት ውስጥ በስርዓተ ትምህርት እና ፈተና ዝግጅት ከፍተኛ ልምድ ያካበቱ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ምሁራን፣ የሙያ ማህበራት ተወካዮች እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላት አስፈላጊውን ግብዓት የሰጡበት መሆኑ ተገልጿል፡፡

የፈተና ማስፈጸሚያ መመሪያው በፍትህ ሚኒስቴር ተመዝግቦ እና ጸድቆ ለትግበራ ይፉ መደረጉ ነው የተጠቆመው፡፡

የጸደቀው መመሪያ ከሚቀጥለው የትምህርት ዘመን ጀምሮ ተግባራዊ እንዲሆን ለሁሉም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መላኩን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.