Fana: At a Speed of Life!

በዳኝነት አካል ውስጥ የሙስና መከላከያ ስትራቴጂ መመሪያ ጸደቀ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)የፌደራል ዳኞች አስተዳደር ጉባኤ የፌደራል ፍርድ ቤቶች በዳኝነት አካል ውስጥ የሙስና ተግባራት መከላከያ እና መቆጣጠሪያ ስትራቴጂ ማስፈጸሚያ መመሪያን አጸደቀ፡፡

ጉባኤው ዛሬ ባደረገው መደበኛ ስብሰባ ነው የፌደራል ፍርድ ቤቶች በዳኝነት አካል ውስጥ የሙስና ተግባራት መከላከያ እና መቆጣጠሪያ ስትራቴጂ ማስፈጸሚያ መመሪያን ያጸደቀው፡፡

የህግ ማዕቀፉ የፌደራል ፍርድ ቤቶች ውስጥ አሰራር፣ አደረጃጀት እና ስልቶችን በመዘርጋት እንዲሁም በህግ ስልጣን ካላቸው ሌሎች አካላት ጋር ቅንጅት የሚፈጠርበትን አሰራር በመዘርጋት የዳኝነት ነጻነትን ሙሉ በሙሉ ባስጠበቀ መልኩ የተዘጋጀ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ከዚህ ባለፈም መመሪያው በዳኝነት አካሉ ውስጥ የሙስና ተግባራትን የሚፈጽሙ ዳኞችና የጉባኤ ተሿሚዎች ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ ታስቦ መጽደቁን ከፌደራል ዳኞች አስተዳደር ጉባኤ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.