Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ እና በቻይናዋ ሄይሎንግጂያንግ ግዛት መካከል አጋርነት ተመሰረተ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አምባሳደር ተሾመ ቶጋ በኢትዮጵያ እና በቻይናዋ ሄይሎንግጂያንግ ግዛት መካከል አጋርነት መመሥረት ያስቻለ የሁለት ቀናት ጉብኝት ማካሄዳቸውን ገለጹ፡፡

አምባሳደር ተሾመ ቶጋ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት፣ የንግድና የኢንቨስትመንት ትሥሥር እንዲሁም የነጻ የትምህርት ዕድል ፕሮግራሞችን እና ተያያዥ ጉዳዮች ማመቻቸት የሚያስችል አጋርነት መመሥረቱን ገልጸዋል፡፡

አምባሳደር ተሾመ ቶጋ በጉብኝታቸው ከሄይሎንግጂያንግ ግዛት ምክትል አስተዳዳሪ ዋንግ ይሺን ፣ከሃርቢን ከተማ ምክትል ከንቲባ ጉዎ ሹንሚን፣ ከሀገሪቷ ጠቅላይ ግዛት የውጭ ጉዳይ ጽኅፈት ቤት ዳይሬክተር ው ዌን እና ከሌሎች የቻይና ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጋር ተገናኝተው የሁለትዮሽ ውይይት ማድረጋቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።

አምባሳደር ተሾመ ቶጋ በ2022 የዓለም የ5ኛው ትውልድ ኮንቬንሽን የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ላይም ተጋብዘው በክብር እንግድነት መገኘታቸው ተጠቁሟል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.