Fana: At a Speed of Life!

የሀገር ውስጥ መድሃኒት አምራቾችና አቅራቢዎች ምርታማነትና አቅርቦት መዳከሙ ተነገረ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)የሀገር ውስጥ መድሃኒት አምራቾችና አቅራቢዎች ምርታማነትና አቅርቦት ካለፉት 5 ዓመታት ጋር ሲነጻጸር በከፍተኛ ሁኔታ መዳከሙ ተገለጸ፡፡

የኢትዮጵያ መድሃኒት አቅራቢ አገልግሎት ይህን የገለጸው ከሀገር ውስጥ መድሃኒት አቅራቢዎችና አምራቾች ጋር ዓመታዊ የሕክምና ግብዓቶች አቅርቦት አፈጻጸም ላይ ባካሄደው ውይይት ነው፡፡

አገልግሎቱ በዚህ ዓመት የ14 ቢሊየን ብር የሕክምና ግዓቶች ግዢ ያከናወነ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 1 ነጥብ 2 ቢሊየኑ ብቻ በሀገር ውስጥ አምራቾች መሸፈኑ ተገልጿል፡፡

የሀገር ውስጥ መድሃኒት አምራቾችንና አቅራቢዎችን በ10 ዓመታት ውስጥ ወደ 60 በመቶ ለማሳደግ ቢታቀድም በተለያዩ ምክንያቶች አቅማቸው ከዕለት ወደ ዕለት እየወረደ ሥምንት በመቶ ያህሉን ብቻ እየሸፈኑ እንደሚገኙም ነው በውይይቱ ላይ ተነስቷል፡፡

የኢትዮጵያ መድሃኒት አቅራቢ አገልግሎት ለ5ሺ ጤና ጣቢያዎች በቀጥታ የሕክምና ግብዓቶችን ተደራሽ ያደርጋል፡፡

በዘቢብ ተክላይ

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.