Fana: At a Speed of Life!

የታቀደውን የወጪ ንግድ ለማሳካት በትኩረት ይሰራል – ሚኒስቴሩ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከላኪዎቸ ጋር ተቀራርቦ በመስራት የታቀደውን የወጪ ንግድ ለማሳካት በትኩረት እንደሚሰራ የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ገለጸ፡፡

ሚኒስቴሩ ከጥራጥሬ እና ከቅባት እህል ላኪዎች ጋር የወጪ ንግድ ገቢን ለማሳደግ በሚቻልበት አግባብ ላይ እየተወያየ ነው፡፡

በበጀት ዓመቱ የተያዘውን የወጪ ንግድ እቅድ ለማሳካት በተሰራ ስራ 4 ነጥብ 12 ቢሊየን ዶላር ገቢ ማግኘት እንደተቻለ ተገልጿል፡፡

ከገቢው ውስጥ 906 ሚሊየን ዶላሩ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ከሚከታተላቸው ዘርፎች የተገኘ ነው ተብሏል፡፡

በ2015 በጀት ዓመት የተያዘውን 5 ነጥብ 4 ቢሊየን ዶላር ገቢ እቅድ ለማሳካት የዘርፉን ችግር በመፍታት እና የወጪ ንግድ ላኪዎችን በማሳተፍ በትኩረት እንደሚሰራ የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ካሳሁን ጎፌ ገልጸዋል፡፡

በበጀት አመቱ የመጀመሪያ ወር ከታቀደው ዕቅድ ውስጥ ከቅባት እህሎች 136 በመቶ ገቢ ተገኝቷል ማለታቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ይህም በበጀት ዓመቱ የተያዘውን እቅድ ለማሳካት እየተደረጉ ያሉ ጥረቶችን ውጤታማነት ሊያሳይ የሚችል ነው ተብሏል፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.