Fana: At a Speed of Life!

ቴክኖሎጂ መር ሥራ ፈጣሪ ሴቶችን የሚደግፍ መርሐ-ግብር በኢትዮጵያ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሴቶች የሚመሩ እና በሃሳብ ደረጃ ያሉ አዲስ የቴክኖሎጂ መር ሥራ ፈጠራዎችን የሚደግፍ “ቴክ አፍሪካ ውመን” የተሰኘ መርሐ-ግብር በኢትዮጵያ ተጀመረ፡፡

በተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ድጋፍ በ“ቤታ ኪዩብ” መሪነት ነው የሚተገበረው።

መርሐ-ግብሩ ሴቶች ሊጀምሯቸው ያሰቧቸውን አዲስ ቴክኖሎጂ መር ሥራ ፈጠራ ፕሮጀክቶች ወደ መሬት እንዲያወርዷቸው እና እንዲተገብሯቸው ያስችላል ተብሏል፡፡

“ቴክ አፍሪካ ውመን” ሥራ ፈጣሪ ሴቶች ከአፍሪካ አቻዎቻቸው ጋር የንግድ ሽርክና እንዲፈጥሩ ፈንዶችን በማፈላለግ እንደሚደግፍ ተጠቁሟል፡፡

በቴክ አፍሪካ መርሐ-ግብር በኢትዮጵያ፣ ሴኔጋል፣ ታንዛኒያ እና ቱኒዚያ የሚገኙ ሴት የሥራ ፈጠራ ፕሮጀክት ሃሳብ አመንጪዎችን በአባልነት ለማቀፍ ማመልከቻቸውን እስከ ነገ ድረስ በበይነ-መረብ እንዲያቀርቡ ጋብዟል፡፡

ሴት ተመዝጋቢዎች ከቴክኖሎጂ ገንቢዎች እና ዲዛይነሮች እንዲሁም ከግብይት እና ፋይናንስ ባለሙያዎች የመገናኘት ዕድል እንደሚፈጠርላቸው ተመላክቷል፡፡

ምርጥ ሁለት የሴቶች ሥራ ፈጠራ ፕሮጀክቶች ከየሀገራቱ በተለያዩ ውድድሮች ተለይተው አሸናፊዋ ሴት 7 ሺህ የአሜሪካ ዶላር እንደምትሸለም መጠቆሙን ዲስራፕት አፍሪካ ዘግቧል፡፡

 

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.