Fana: At a Speed of Life!

በአፍሪካ ፍትሃዊ የክትባት ስርዓት እንዲዘረጋ ጥሪ ቀረበ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፍሪካ ወረርሽኞችን ለመከላከል ተጨማሪ ክትባቶችን ለማምረት “የቴክኖሎጂ መጋራት” እና “የፈጠራ ድጋፍ” እንዲደረግ ጥሪ ቀረበ።
የፈረንሳይ፣ የጀርመን፣ የሩዋንዳ፣ የደቡብ አፍሪካ፣ የሴኔጋል ፕሬዝዳንቶች እና የዓለም ጤና ድርጅት በሌ ሞንድ ባወጡት መግለጫ ስጋታቸውንን አንስተዋል።
ሊፈጠር የሚችል ተላላፊ ወረርሽኞችን ቀውስ በተሻለ ሁኔታ ለመከላከል ትብብርን ማጎልበት፣ በአገር ውስጥ በተመረቱ ምርቶች ላይ እምነት ለመፍጠር ጊዜው አሁን ነው ሲሉም አበክረው ተናግረዋል።
በ2024 መጀመሪያ ላይ በአህጉሪቱ በሚሊዮን ለሚቆጠሩ ሰዎች ለኮቪድ-19 እና ለሌሎች በሽታዎች ክትባቶችን ለማምረት ዓላማ ያነገበው በአፍሪካ የመጀመሪያ የሆነው አር ኤን ኤ የክትባት ማምረቻ ፋብሪካ በሰኔ ወር በሩዋንዳ መከፈቱም ተገልጿል።
ደቡብ አፍሪካም በጥር ወር የኮቪድ ክትባት ፋብሪካ ያቋቋመች ሲሆን፥ ሴኔጋል የክትባት ማምረት ክልላዊ ማዕከል ለመሆን መዘጋጀቷ ተጠቁሟል።
የፎረሙ ፈራሚዎች “የክትባት ማምረቻ ማዕከል መገንባት አስቸጋሪ ነው ፤ ዘላቂነቱን ማረጋገጥ ደግሞ የበለጠ ከባድ ነው” ማለታቸውም ተጠቅሷል።
በአፍሪካ እና በሌሎች የዓለም ክፍሎች የሚከሰቱ ወረርሽኞችን ለመከላከል ሰፊ የሠራተኞች ስልጠና፣ የተሻለ ደንብ እና ተጨማሪ መዋዕለ ንዋይ ፈሰስ እንዲደረግም ጠይቀዋል።
የኤም አር ኤን ቴክኖሎጂ “እንደ ኤች አይ ቪ ኢንፌክሽን፣ ሳንባ ነቀርሳ፣ ወባ እና ሌሎች በሽታዎችን ለመዋጋት ትልቅ አቅም እንደሚኖረውም” መናገራቸውን የአፍሪካ ኒውስ ዘገባ አመላክቷል።
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.