Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ ነገ በአንድ ጀምበር 4 ሚሊየን ችግኝ ይተከላል

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በነገው ዕለት በአዲስ አበባ ከተማ በአንድ ጀምበር አራት ሚሊየን ችግኝ የመትከል መርሐ ግብር እንደሚካሄድ ተገለጸ፡፡
አረንጓዴ አሻራ የማሳረፍ መርሐ ግብሩ በአዲስ አበባ ከተማ በ11ዱም ክፍለ ከተሞች ከጠዋቱ 12 ሰዓት ጀምሮ እንደሚካሄድ ከከንቲባ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
በዕለቱም ወጣቶች፣ ተማሪዎች፣ የፀጥታ አካላት፣ የእምነት አባቶች፣ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች፣ ባለሃብቶች፣ በጎ ፈቃደኞች እና ሁሉም የከተማዋ ነዋሪ በየክፍለ ከተማው ለችግኝ መትከያ በተዘጋጁ ቦታዎች ላይ ደማቅ አረንጓዴ አሻራውን እንዲያሳርፍ ጥሪ ቀርቧል፡፡
 
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
 
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.