Fana: At a Speed of Life!

በማስፈራራት 260 ሺህ ብር የተቀበሉ የፌደራል ፖሊስ ሰራተኞች በእስራት ተቀጡ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከኢንሳ ነው የመጣነው ብለው በማስፈራራት 260 ሺህ ብር የተቀበሉ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ሰራተኞች በእስራት ተቀጡ፡፡

የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን አባላቶቹ በመመሳጠር የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ተገን በማድረግ እና ስልጣናቸውን አላግባብ ተጠቅመው በፈፀሙት ወንጀል ነው በእስራት የተቀጡት፡፡

ተከሳሾቹ የግል ተበዳይን “ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ነው የመጣነው፤ ለወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ለጥያቄ እንፈልግሃለን” በማለት የግል ተበዳይን ከሱቁ በማስወጣት ለገሃር አካባቢ መውሰዳቸው በችሎቱ ተረጋግጧል፡፡

በኋላም አንድ ሚሊየን ብር አምጣ ካልሆነ ለኦሮሚያ ፖሊስ አሳልፈን እንሰጥሃለን በማለት 260 ሺህ ብር ወደ ሂሳብ ደብተራቸው እንዲያስተላልፍ ካደረጉ በኋላ ገንዘቡን በመከፋፈል ለግል ጥቅማቸው አውለዋል፡፡

ጉዳዩን ሲከታተል የነበረው በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 4ኛ ወንጀል ችሎት ተከሳሾቹ ጥፋተኛ መሆናቸውን ካረጋገጠ በኋላ አራቱም ተከሳሾች እያንዳንዳቸው በ3 ዓመት ፅኑ እስራት እና 2 ሺህ ብር እንዲቀጡ መወሰኑን ከፍትህ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.