Fana: At a Speed of Life!

የኦሮሚያ ክልል ላጋጠሙት ፈተናዎች እጅ ሳይሰጥ ታሪክ የሚያስታውሳቸውን ድሎች አስመዝግቧል – የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ክልል ላጋጠሙት ፈተናዎች እጅ ሳይሰጥ ታሪክ የሚያስታውሳቸውን ድሎች እያስመዘገበ ዛሬ ላይ ደርሷል ሲል የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት አስታወቀ።

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት 30ኛ ዓመት የምሥረታ በዓሉን አስመልክቶ መግለጫ አውጥቷል፡፡

መግለጫው ከሠላሳ ዓመት በፊት ኦሮሚያ የሚባል ክልል እንዳልነበረና በተከፈለ የሕዝቦች መሥዋዕትነት ኦሮሚያን ዕውን ማድረግ እንደተቻለ አውስቷል፡፡

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ነሐሴ 13 ቀን 1984 ዓ.ም መመሥረቱንም መግለጫው ጠቁሟል፡፡

መግለጫው የኦሮሞ ህዝብ በተለያዩ ወቅቶች ያጋጠሙትን የጭቆና ቀንበሮች እና ሕዝብን ከሕዝባ የማጫረስ አጀንዳዎች በከፈለው መሥዋዕትነት እየመለሰ ዛሬ ለደረሰበት የትምህርት፣ የኢኮኖሚ፣ የፖለቲካ እና የማኅበረሰብ ልማት መብቃቱን አንስቷል፡፡

የኦሮሞ ሕዝብ አፋን ኦሮሞ የመናገር፣ ቴክኖሎጂ የመጠቀም ፣ ባሕሉን የማሳደግ እና ሃሳቡን በነጻነት የመግለጽ ነጻነት የተከለከለበት ዘመን እንደነበርም መግለጫው አስታውሷል።

ዛሬ ላይ ግን ቀድመው እንደ ጀኔራል ዋቆ ጉቱ ያሉ ጀግኖች በከፈሉት መሥዋዕትነት ሳይንስና ቴክኖሎጂን የተማረ የቁቤ ትውልድ ድርብ ድል ማስመዝገቡን ገልጿል፡፡

የኦሮሞ ሕዝብ ራስን በራስ የማስተዳደር ጥያቄው፣ ባሕሉን፣ ቋንቋውን፣ ታሪኩንና ወጉን የማልማት መብቱና ጥቅሙን ሁሉ ማስከበር መቻሉንም ነው መግለጫው ያነሳው፡፡

ዛሬ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት 30ኛ ዓመት የምሥረታ በዓል የሚያከብረው የትናንቱን መጥፎ ታሪክና ጠባሳ እያሰበ ሳይሆን የኢትዮጵያን ቀጣይ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊ እና ማኅበራዊ የስኬት መንገዶች ከግብ ለማድረስ ሌት ተቀን ጠንክሮ እየሠራ መሆኑ ተገልጿል፡፡

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በሀገሪቱና በክልሉ የተከሰተውን የሰላምና ያለመረጋጋት ችግር ለመመለስ እንደሚተጋ መግለጹን ከኦሮሚያ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.