Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያና ኡጋንዳ የናይል የጋራ ተጠቃሚነት የመግባቢያ ሰነድን ያላፀደቁ አገራት እንዲያፀድቁ ጥሪ አቀረቡ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ እና ኡጋንዳ የናይል ተፋሰስ አባል ሀገራት የጋራ ተጠቃሚነት የመግባቢያ ሰነድን ያላፀደቁ አገራት እንዲያፀድቁ ጥሪ አቀረቡ።

 

በታንዛኒያ፣ ዳሬ ሰላም የተፋሰሱ አገራት የሚኒስትሮች ጉባኤ ተካሂዷል።

 

በጉባኤው ላይ የተሳተፉት የኢፌዴሪ የውኃ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ሀብታሙ ኢተፋ እና የኡጋንዳ የውኃ እና አካባቢ ጥበቃ ሚኒስትር ሳም ቸፕቶሪስ ናቸው ።

 

በጉባኤው የተሳተፉት በታንዛኒያ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ሽብሩ ማሞ እንደገለፁት፥ ጥሪውን ያቀረቡት ኢትዮጵያ እና ኡጋንዳ የናይል ተፋሰስ አገራት በጋራ ለመልማት የታቀደውን ኮሚሽን ለማሳደግ እንደሚሰሩ ገልጸዋል።

 

በታንዛኒያ ዳሬ ሰላም በተካሄደው የተፋሰሱ የሚኒስትሮች ጉባኤ እንደተገለጸው ከግብፅ በስተቀር  ሁሉም የተፋሰሱ አገራት ተጋግዘው በአንድነት ለመስራት ተስማመተዋል።

 

በታንዛኒያ ዳሬ ሰላም ለአንድ ቀን የተካሄደው የናይል ተፋሰስ አገራት የሚኒስትሮች ጉባኤ መጠናቀቁን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.