Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ የላቀ የገቢ አፈፃፀም ያስመዘገቡ ተቋማት ዕውቅና እና ሽልማት አገኙ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ በ2015 በጀት ዓመት ሐምሌ ወር የላቀ ገቢ አፈፃፀም ላበረከቱ ባለድርሻ አካላት የዕውቅና እና የሽልማት መርሐ ግብር አካሄደ።

በመርሐ ግብሩ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የቢሮው ኃላፊ አቶ ሙሉጌታ ተፈራ እንደተናገሩት ፥ ተቋሙ በሐምሌ ወር 2015 በጀት ዓመት 8 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ አቅዶ፥ 8 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር ወይም የዕቅዱን 107 ነጥብ 6 በመቶ የገቢ አፈፃፀም አስመዝግቧል።

ይህም ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ2 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር (የ35.5 በመቶ) እድገት አሳይቷል።

የገቢ አሰባሰቡ በታቀደው መሰረት ግቡን እንዲመታ ተልዕኳቸውን በአግባቡ ለተወጡ ባለድርሻ አካላት
የዕውቅና እና ሽልማት መርሐ ግብሩ የተዘጋጀ መሆኑን የገለጹት የቢሮው ኃላፊ፥ መሰል የማበረታቻና የእውቅና ፕሮግራምች ተጠናክረው ይቀጥላሉ ማለታቸውን ከቢሮው ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል።

በመርሐ ግብሩ ላይ የአዲስ አበባ ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴዎች፣ የቢሮው ኃላፊዎች፣ የክፍለ ከተማ ስራ አስፈፃሚዎች፣ የነጋዴዎች ፎረምና የፖሊስ ተወካዮች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.