Fana: At a Speed of Life!

የኡጋንዳ የልዑካን ቡድን ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገባ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 15 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኡጋንዳ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ኦኬሎ ኦሪየም እንዲሁም የሀገሪቱ የምድር ኃይል ዋና አዛዥና የፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ የልዩ ዘመቻ ከፍተኛ አማካሪ ሌተናል ጀነራል ሙሆዚ ኪኑሩጋባን ጨምሮ ሌሎች የደኅንነትና ወታደራዊ ከፍተኛ አመራሮችን ያካተተው የልዑካን ቡድን ዛሬ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገብቷል፡፡

ለልዑካ ቡድኑ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ጀነራል አቶ ተመስገን ጥሩነህን ጨምሮ የአገልግሎት መሥሪያ ቤቱ ከፍተኛ አመራሮች አቀባበል አድርገውለታል።

የልዑካን ቡድኑ በሚኖረው ቆይታ ከኢትዮጵያ አቻው ጋር ኢትዮጵያን እና ኡጋንዳ በምሥራቅ አፍሪካ ሰላምና ደኅንነት ለማረጋገጥ እንዲሁም ሽብርተኝነትን ለመከላከል የሚያደርጓቸውን የትብብር ሥራዎች ለማጠናከር የሚያግዝ ውይይት ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል ፡፡

የኡጋንዳ ጦር የምድር ኃይል ዋና አዛዥና የፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ የልዩ ዘመቻ ከፍተኛ አማካሪ ሌተናል ጀነራል ሙሆዚ ኪኑሩጋባ የኡጋንዳ ፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ ልጅ መሆናቸው እንደሚታወቅ የብሄራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ለመገናኛ ብዙሃን በላከው መረጃ አመላክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.