Fana: At a Speed of Life!

የሻደይ በዓል በሰቆጣ ከተማ በድምቀት መከበር ጀምሯል

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሻደይ በዓል በአማራ ክልል ሰቆጣ ከተማ እንደ ሀገር በድምቀት መከበር ጀምሯል።

በበዓሉ ላይ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንንን ጨምሮ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች እየተሳተፉ ነው።

በተጨማሪም ከሀገሪቱ የተውጣጡ እንግዶች በሰቆጣ ከተማ በድምቀት እየተከበረ በሚገኘው የሻደይ በዓል ታድመዋል።

በዓሉ በየዓመቱ በወርሀ ነሐሴ የሚከበር ሲሆን÷ በተለይ ሴት ወጣቶች የሻደይን ጨዋታ እየተጫወቱ ያሳልፋሉ።

በታሪኩ ለገሰ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.