Fana: At a Speed of Life!

ለኮ/ል አማረ ሞላ መሰናዶ ት/ ቤት የማስፋፊያ ግንባታ የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሰቆጣ ከተማ ለሚገኘው ኮሎኔል አማረ ሞላ መሰናዶ ትምህርት ቤት ሙሉ የማስፋፊያ ግንባታ የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ፡፡

የመሰረት ድንጋዩን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ፣ የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እንዲሁም ሌሎች ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች አስቀምጠዋል፡፡

በመርሐ ግብሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እንደገለጹት ÷ ግንባታው በ2015ዓ.ም ተጠናቆ በ2016 ዓ.ም አገልግሎት መስጠት ይጀምራል፡፡

ሚኒስትሩ የአካባቢው ማህበረሰብ ለትምህርት ቤቱ የመጫወቻ ሜዳ፣ አጥር እና ሌሎች አስፈላጊ ነገሮችን የማሟላት ሃላፊነት እንዳለበት መናገራቸውን ከሰቆጣ ከተማ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

አቶ ደመቀ መኮንን በበኩላቸው÷ በአዲሱ አሰራር መሰረት ድንጋይ ማስቀመጥ ብቻ ሳይሆን ግንባታዎችን በአጭር ጊዜ ውስጥ አጠናቆ አገልግሎት እንዲሰጡ ማድረግ እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡

 

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.