Fana: At a Speed of Life!

የኔዘርላንድስ ባለሃብቶች በግብርና ዘርፍ ለመሰማራት ፍላጎት እንዳላቸው ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኔዘርላንድስ ባለሃብቶች በኢትዮጵያ በአትክልት፣ ፍራፍሬ እና ቡና ኢንቨስትመንት ለመሳተፍ ፍላጎት እንዳላቸው የሀገሪቱ አምባሳደር ሄንክ ጃር ገለጹ።

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ነጋሽ ዋጌሾ በኢትዮጵያ የኔዘርላንድስ አምባሳደር ሄንክ ጃር ባካርን ዛሬ በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።

አምባሳደሩ የሀገራቸውን የተለያዩ ባለሃብቶች በመጋበዝ ክልሉን እንዲጎበኙ ጥረት እንደሚያደርጉም ተናግረዋል ።

በሆልቲካልቸር ልማትና በቡና ኢንቨስትመንት ላይ የሀገራቸው ባለሃብቶች ለማልማት ፍላጎት እንዳላቸውም አምባሳደር ሄንክ ጃር ገልጸዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ በበኩላቸው ፥ የኔዘርላንድስ ባለሀብቶች በክልሉ በተለያዩ የኢንቨስትመንት አማራጮች ሲሳተፉ አስፈላጊውን ድጋፍ የክልሉ መንግስት እንደሚያደርግ መግለጻቸውን ከክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.