Fana: At a Speed of Life!

ለኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ከ70 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ለኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ከ70 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለው የአምቡላንስና ሌሎች ግብዓቶች ድጋፍ ተደረገ።

ድጋፉን ዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ እና የኔዘርላንድስ እንዲሁም የኦስትሪያ ቀይ መስቀል ማህበራት ናቸው ያበረከቱት።

ድጋፉ 20 አምቡላንሶች፣ 19 ቀላል ተሽከርካሪዎች እና 25 ጄነሬተሮች ያካተተ ሲሆን÷በዋናነት ግጭትና የተፈጥሮ አደጋ በተከሰተባቸው አካባቢዎች ላሉ የጤና ተቋማት ተደራሽ የሚሆኑ ናቸው ተብሏል።

የዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ የኢትዮጵያ ልዑክ ኃላፊ ኒኮላስ ቮን አርክስ÷ ድጋፉ በበግጭትና በተፈጥሮ አደጋ ሳቢያ የሕክምና ቁሳቁስ እጥረት ያጋጠማቸውን የአገሪቱ አካባቢዎች ታሳቢ በማድረግ የተለገሰ ነው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ዋና ፀሐፊ አቶ ጌታቸው ታዓ በበኩላቸው÷ ድጋፉ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች እንዲሁም ጦርነቱ ተከስቶባቸው በነበሩ አካባቢዎች ላሉ የጤና ተቋማት አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ገልጸዋል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.