Fana: At a Speed of Life!

የበጎ ፍቃድ አገልገሎትን አንድነትን ለማጠናከር መጠቀም እንደሚገባ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የክረምት በጎ ፍቃድ አገልገሎትን ኢትዮጵያዊ አንድነትን ለማጠናከር በሚያስችል መልኩ መጠቀም እንደሚገባ የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ ገለፁ።

ርዕሰ መስተዳድሩ የክልሉ የትምህርት ፣ ባህልና ቱሪዝም ፣ ፋይናንስ ፣ እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢዎች እና የሌሎችን ተቋማት የክረምት በጎ ፍቃድ አተገባበር ተመልክተዋል፡፡

በዚህ ወቅት ርዕሰ መስተዳድሩ አቶ ኡሞድ እንዳሉት ÷ ሴክተር ቢሮዎች በፍቃደኝነት ላይ የተመሰረተ ተሳትፎ በማድረግ ለሚኖሩበት ማህበረሰብ ሰፊ የልማት አውታሮችን በመዘርጋት የዜግነት ኃላፊነትን መወጣት ይኖርባቸዋል።

በተለይም የክረምት በጎ ፍቃድ ሥራ ሀገራዊና ብሔራዊ ግዴታዎችን የሚያውቁበት በማህበራዊ ተግባራቸው ግንባር ቀደም የሚሆኑና የሀገርና የወገን ፍቅርን የሚያዳብሩበት ትልቅ ሚና ያለው ተግባር እንደሆነ አስታውቀዋል።

የአቅመ ደካሞችንና የአረጋውያንን የመኖሪያ ቤት መጠገን፣ የአካባቢ ጽዳት፣ ችግኝ ተገላ፣ የዝቅተኛ ነዋሪ ተማሪዎችን የትምህርት ቁሳቁስ ማሟላት በክረምቱ ትኩረት ተሰጥቶ የሚሰራባቸው ጉዳዮች እንደሆኑም መጠቆማቸውን ከጋምቤላ ክልል የመንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.