Fana: At a Speed of Life!

በቀን እስከ 1 ሺህ 500 የኦንላይን የቪዛ አገልግሎት እየተሰጠ መሆኑ ተገለጸ

 

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦንላይን አገልገሎት ከተጀመረ ቅርብ ጊዜ ቢሆነውም በቀን ከ800 እስከ 1ሺህ 500 የሚደርስ የኦላይን የቪዛ አገልግሎት እየተሰጠ መሆኑ ተገለጸ፡፡

በቆንስላ፣ ኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ኦንላይን የሚቀርቡ አማራጭ አገልግሎቶች ላይ ውይይት ተካሄዷል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ብርቱካን አያኖ በውይይቱ ላይ እንደገለጹት÷ የኢሚግሬሽን እና ቆንስላ አገልግሎት አሰጣጥን በማዘመን ጥራትና ፍጥነትን መሰረት በማድረግ መፈፀም ይገባል፡፡

ቴክኖሎጂን በመጠቀም አገልግሎቶች ቀልጣፋ እንዲሆኑ አማራጭ የኦንላይን አገልግሎት ለተገልጋዮች መቅረቡን ጠቁመው÷ በአሠራር ሂደት ለሚታዩ ችግሮች መፍትሔ መስጠት ይገባል ብለዋል።

የኢምግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ብሩህ ተስፋ÷ በተገልጋዮች በሚቀርቡ የአገልግሎት ጥራት ችግር እና እየተተገበረ በሚገኘው የኦንላይን አገልግሎት ላይ የሚነሱ ቅሬታዎች በዘላቂነት መፍትሔ ለመስጠት በትብብር እንሠራለን ብለዋል።

የኦንላይን አገልገሎት ከተጀመረ ቅርብ ጊዜ ቢሆነውም በቀን ከ800 እስከ 1ሺህ 500 የሚደርስ የኦንላይን የቪዛ አገልግሎት እየተሰጠ ነው ማለታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል፡፡

የውይይቱ ተሳታፊ አምባሳደሮች በሰጡት አስተያየት፥ ኢ-ቪዛ ለማግኘት ያመለከቱ ደንበኞች በሀሰተኛ ድረገጾች እንዳይታለሉ ኤምባሲዎችን እና ሚሲዮኖችን መጠየቅ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.