Fana: At a Speed of Life!

በድሬዳዋ የተገነባው የኦክስጂን ማምረቻ እና ማከፋፈያ ፋብሪካ ተመረቀ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር በ50 ሚሊየን ብር ወጪ የተገነባው የኦክስጂን ማምረቻ እና ማከፋፈያ ፋብሪካ ተመረቀ።

ፋብሪካው በየአብሥራ ኢንዱስትሪያል ኮምፕሌክስ አማካኝነት የተገነባ መሆኑ ታውቋል።

ፋብሪካውን የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር፣ የየአብሥራ ኢንዱስትሪያል ኮምፕሌክስ ባለቤት አቶ የአብስራ በለጠ እና የአስተዳደሩ የካቢኔ አባላት መርቀው ከፍተውታል።

ፋብሪካው በቀን 520 ሲሊንደር ኦክሲጂን የማምረት አቅም አለው ተብሏል።

የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር በዚሁ ጊዜ እንዳሉት የፋብሪካው መገንባት በአስተዳደሩ የነበረውን የህክምና ኦክስጂን እጥረት ለመቅረፍ የሚረዳ ነው።

ከዚህ በፊት ኦክሲጂን ለማግኘት አዲስ አበባ ድረስ ይኬድ እንደነበረ አስታውሰው ፋብሪካው ይወጣ የነበረውን ጉልበትና ወጪ እንደሚቀንስ መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.