Fana: At a Speed of Life!

ከ423 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው 69 ተሽከርካሪዎች ለክልሎች ተከፋፈሉ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከ423 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው 69 የመስክ ተሽከርካሪዎችን ለክልሎች አከፋፈለ፡፡

በርክክብ መርሐ ግብሩ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር አስፋው ዲንጋሞ እንደገለጹት÷ ተሽከርካሪዎቹ በየክልሎቹ ውሃ፣ ጤናና ትምህርት ቢሮዎች በአንድ ቋት መጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ፕሮግራም ለሚገነቡ ተቋማት ክትትልና ድጋፍ ለማድረግ ታሳቢ የተደረጉ ናቸው ብለዋል፡፡

ተሽከርካሪዎቹ የክልሎችን አቅም ለማጠናከር በሁለተኛው ምዕራፍ የአንድ ቋት መጠጥ ውሃ ሳኒቴሽንና ሀይጂን ፕሮግራም የተገዙ መሆናቸውንም ተናግረዋል፡፡

ሁለተኛው የከተሞች መጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ፕሮግራም በኢትዮጵያ በሁሉም ክልሎች በ355 ወረዳዎች እየተተገበረ መሆኑን ከሚስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.