Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የምስጋና መርሐ ግብር አካሄደ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በ2014 በጀት ዓመት ለነበረው ውጤታማ ጊዜ ከጎኑ ለነበሩ ተቋማትና ባለድርሻ አካላት የምስጋና መርሐ ግብር አካሄደ፡፡

በመርሐ ግብሩ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር አቶ ቀጀላ መርዳሳ ፣ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ዴኤታዎች አምባሳደር መስፍን ቸርነት እና ወ/ሮ ወርቅነሽ ብሩ፣ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አትሌት ደራርቱ ቱሉ ፣ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት፣ የተለያዩ ተቋማት የስራ ኃላፊዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት አትሌት ደራርቱ ቱሉ ፥ “ፌዴሬሽኑ በታሪኩ በ2014 ዓ.ም ከሌሎች ጊዜያት በአህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ውድድሮች አመርቂ ውጤትን ሲያስመዘግብ ከፌዴሬሽኑ ጎን በመሆን ለስኬቱ ድጋፍ ያደረጉ ተቋማትና ባለድርሻ አካላትን እናመሠግናለን” ብላለች፡፡

“ለወደፊትም ተባብረን ከአሁኑ የተሻለ ውጤት በማስመዝገብ ለሀገራችን የተሻለውን እንሰራለን የሚለውን ለማመልከትና የአብሮነት ጉዟችን እንደከዚህ ቀደሙ እንዲቀጥል ነው” ስትልም ነው የገለጸችው።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.