Fana: At a Speed of Life!

በባለልዩ ጣዕም የቡና ቅምሻ አንድ ኪሎ የኢትዮጵያ ቡና በ47 ሺህ 236 ብር ተሸጠ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ለሦስተኛ ጊዜ ሲካሄድ የቆየው የባለልዩ ጣዕም የቡና ቅምሻ (ካፕ ኦፍ ኤክሰለንስ) ውድድር የኢትዮጵያ ቡና አሸነፈ፡፡

የኢትዮጵያ ቡና እና ሻይ ባለስልጣን “ቡናችን ዳግም አሸነፈ፤ አርሶ አደሮቻችንም አሸንፈው የኢትዮጵያ ኩራት ሆነዋል” ብሏል፡፡

በዘንድሮው የባለልዩ ጣዕም የቡና ቅምሻ 2022 ውድድር ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ በጥራቱ በአንደኝነት ከፍተኛ ነጥብ መመዝገቡን ባለስልጣኑ አስታውቋል፡፡

ከትናንትና ምሽት ጀምሮ በተከናወነው ዓለም ዓቀፍ ኦንላይን ጨረታ እጅግ በሚያስደንቅ ሁኔታ አንድ ኪሎ ግራም ቡና 884 ነጥብ 10 ዶላር ወይም 47 ሺህ 236 ነጥብ 23 ብር ተሸጧል ነው ያለው፡፡

ይህ ዋጋ ለአንድ የኢትዮጵያ ቡና የተሰጠ አስደናቂ ዋጋ መሆኑን የባለስልጣኑ መረጃ አመላክቷል፡፡

ይህ ስኬት እንዲመዘገብ ላስቻሉ ሁሉም አካላት ባለስልጣኑ አመስግኗል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.