Fana: At a Speed of Life!

የክልሉ መንግስት የአደረጃጀት ጥያቄዎችን ለመመለስ ያደረገው ጥረት የሚበረታታ ነው -አቶ ርስቱ ይርዳ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በበጀት አመቱ የደቡብ ክልል መንግስት የአደረጃጀት ጥያቄዎችን ለመመለስ ያደረገው ጥረት የሚበረታታ መሆኑን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ርስቱ ይረዳ ተናገሩ፡፡

የደቡብ ክልል አመራሮች ያለፈው በጀት አመት አፈጻጸምና የቀጣይ ተግባራት የግምገማ መድረክ በሐዋሳ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ እርስቱ ይርዳ እንዳሉት በበጀት አመቱ የክልሉ ህዝብና መንግሥት የልማትና መልካም አስተዳደር ስራዎችን በተደራጀ መንገድ ለመፈጸም ርብርብ አድርገዋል።

በዚህ ሂደትም ስኬቶችና ጉድለቶች እንደነበሩ ያነሱት አቶ እርስቱ የዚህ መድረክ ዋነኛ አላማም የበጀት አመቱን ስራዎች ገምግሞ በቀጣይ የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ  መሆኑን ተናግረዋል።

በአረንጓዴ አሻራ፣የተጓተቱ ፕሮጀክቶችን በማጠናቀቅ፣ የክልሉን የጸጥታ ሁኔታ ወደ ተሻለ ሁኔታ በማምጣት፣ የህዝቡን የአደረጃጀትናሌሎች የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ለመመለስ የተደረገው ጥረት አበረታች እንደነበርም አንስተዋል።

ለእነዚህ ስኬቶች ተጠናክሮ መቀጠል የአመራሩ ሚናና ቁርጠኝነት  ወሳኝ መሆኑን የገለጹት ርዕሰ መስተዳድሩ፥ የእቅድ አፈጻጸሞችን በተመለከተ በየወቅቱ ግምገማ ማድረግ ይገባል ማለታቸውን የደቡብ ክልል ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.