Fana: At a Speed of Life!

አንድ የሞሮኮ ኩባንያ ለኢትዮጵያ የማዳበሪያ ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሞሮኮው የአፈር ማዳበሪያ አምራች ድርጅት (ኦ ሲ ፒ) የበጋ መስኖ ስንዴ ልማትን ለመደገፍ የሚውል የ50 ሺህ ሜትሪክ ቶን የአፈር ማዳበሪያ ድጋፍ አደረገ፡፡

የኦ ሲ ፒ የአፍሪካ ዋና ስራ አስፈፃሚ መሀመድ አኑዋር ጀማሊ እንደገለጹት÷ ድርጅቱ ኢትዮጵያ የጀመረችውን በስንዴ ልማት ራስን የመቻል ራዕይ ለመደገፍ በማሰብ 50 ሺህ ሜትሪክ ቶን የአፈር ማዳበሪያ (ኤን ፒ ኤስ ቢ) ድጋፍ አድርጓል፡፡

የግብርና ሚኒስትር ዑመር ሁሴን በበኩላቸው ድጋፉ የአፈር ማዳበሪያ አቅርቦት ፈታኝ በሆነበት ጊዜ የተደረገ በመሆኑ ለየት እንደሚያደርገው ጠቁመው፥ ይህም ኢትዮጵያ የጀመረችውን የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት ዕቅድ ለማሳካት በቁርጠኝነት እንድንሠራ ያግዛል ማለታቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ አመላክቷል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.