Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሴቶች እግር ኳስ ቡድን ለፍፃሜ ሳይደርስ ቀረ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሴካፋ ክለቦች ሻምፒዮና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሴቶች እግር ኳስ ቡድን ከዩጋንዳው ሺ ኮርፖሬት ጋር ባደረገው የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ 2 ለ 1 ተሸንፎ  ለፍፃሜ ሳይደርስ ቀርቷል፡፡

ውጤቱን ተከትሎ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅዳሜ ነሐሴ 21 ቀን 2014 ዓ.ም የደረጃ ጨዋታ ያደርጋል።

ሎዛ አበራ ዛሬ ያስቆጠረችውን አንድ ግብ ጨምሮ በውድድሩ ያስቆጠረቻቸውን ግቦች ወደ 10 ከፍ በማድረግ የማጣሪያውን ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነት እየመራች ነው።

የኡጋንዳው ሺ ኮርፖሬትስ የፍጻሜ ጨዋታውን÷ ከታንዛንያው ሲምባ ኩዊንስና ከሩዋንዳው ኤ ኤስ ኪጋሊ አሸናፊ ጋር ያደርጋል።

በታንዛኒያ አስተናጋጅነት እየተካሄደ የሚገኘው የአፍሪካ ሻምፒዮንስ ሊግ የሴካፋ ዞን ማጣሪያ ውድድር ቅዳሜ ነሐሴ 21 ቀን 2014 ዓ.ም ይጠናቀቃል።

የውድድሩ አሸናፊ ሴካፋን ወክሎ በአፍሪካ ሴቶች ሻምፒዮንስ ሊግ እንደሚሳተፍ ኢዜአ ዘግቧል፡፡

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.