Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል ከ5 ሚሊየን በላይ ተማሪዎችን ለመመዝገብ ታቅዷል

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል ከ5 ሚሊየን በላይ ተማሪዎችን ለመመዝገብ ታቅዶ እየተሰራ መሆኑን የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ አስታወቀ፡፡

በ2015 የትምህርት ዘመን እድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ህፃናትን በሙሉ ወደ ትምህርት ቤት መላክ ለሀገር ግንባታ የመሰረት ድንጋይ መጣል መሆኑን የቢሮው ሃላፊ ዶክተር ማተብ ታፈረ ገልጸዋል፡፡

ሃላፊው ዛሬ በእንጅባራ ከተማ ቢሮው ከሚዲያ ባለሙያዎችና አመራሮች ጋር ባደረገው የውይይት መድረክ ላይ እንዳሉት ፥ የወደፊቱ ትልማችን እውን የሚሆነው ትምህርት ላይ በምንሰራው ስራ በመሆኑ ሀገሩን የሚወድ ሁሉ ትምህርት ላይ አበክሮ ሊሰራ ይገባል ብለዋል ።

ሀገር የምንገነባው በለማ የሰው ሀይል በመሆኑ ሁሉም ባለድርሻ አካላት የትምህርት ተሳትፏቸው እንዲያድግና የትምህርት ጥራትን እንዲረጋገጥ በርብርብ መሰራት አለበት ነው ያሉት ።

በትምህርት ስርዓቱ ውስጥ የትምህርት ተሳትፎ እየቀነሰ መጥቷል ያሉት የቢሮ ሃላፊው ፥ ይህም ወላጆች ልጆቻቸውን በተለያየ ምክንያት ልጆቻቸውን ከትምህርት ገበታ እያራቋቸው በመሆኑ የመጣ መሆኑን አመላክተዋል።

የትምህርት ተሳትፎውን በሚያሳድግ መልኩ የ2015 የትምህርት ዘመን የተማሪ ምዝገባ ስራን ለመስራት ከነሐሴ 23 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ጳጉሜን 4 ቀን 2014 ዓ.ም በክልሉ ከ5 ሚሊየን በላይ ተማሪዎችን ለመመዝገብ ታቅዶ ወደስራ መገባቱን አስረድተዋል።

በአበበ የሸዋልዑል

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.