Fana: At a Speed of Life!

በምስራቅ ሐረርጌ እና በሶማሌ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች ከ11 ሺህ በላይ ነዋሪዎችን የንጹህ ውሃ ተጠቃሚ የሚያደርግ ፕሮጀክት ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ በምስራቅ ሐረርጌ ዞን እና በሶማሌ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች የውሃ ምንጮች ላይ 11 ሺህ 700 ነዋሪዎችን የንጹህ መጠጥ ውሃ ተጠቃሚ የሚያደርግ የውሃ መሳቢያ ተከላ ማካሄዱን አስታወቀ፡፡

በምስራቅ ሐረርጌ ዞን እና በሶማሌ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች ያለው የውሃ አቅርቦት በግጭት እና በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት መስተጓጎሉን ኮሚቴው አስታውቋል፡፡

የውሃ አቅርቦቱን ለማሻሻል የዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ በኦርዳ 2 እና 3 እንዲሁም በጎዳኔ 1 እና 2 ቀበሌዎች የውሃ ምንጮች ላይ በፀሐይ ኃይል የሚሠራ የውሃ መሳቢያ ተከላ ማካሄዱን ነው ኮሚቴው የገለጸው፡፡

ይህም 11 ሺህ 700 የአካባቢው ነዋሪዎች ደህንነቱ የተጠበቀ እና ንጹህ ውሃ እንዲያገኙ እንደሚያስችል የኮሚቴው መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.