Fana: At a Speed of Life!

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ነጻነትን በማረጋገጥ ረጋድ ምሁራን ሚናቸውን እንዲወጡ ጥሪ ቀረበ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተቋማዊ ነጻነትን ተግባራዊ በማድረግ ሂደት ውስጥ ምሁራን የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ ትምህርት ሚኒስቴር ጥሪ አቀረበ፡፡

የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ የከፍተኛ  ትምህርት ተቋማት ተቋማዊ ነጻነት ተግባራዊ መደረግ የተቋማትን የውስጥ አቅም ለማሳደግ ሚናው የጎላ መሆኑን በመገንዘብ÷ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ነፃነት ተፈፃሚነት ላይ ሁሉም አካላት የበኩላቸውን አስተዋጾ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተቋማዊ ነፃነት  ተግባራዊ ሲደረግ÷ ተቋማቱ የአመራር፣ አካዳሚያዊ የሰው ኃይል እንዲሁም የገንዘብና ቁሳዊ ሃብት አስተዳደርን በነፃነት እና በተጠያቂነት ለመምራት ያስችላል ብለዋል፡፡

የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከመንግስት  አሠራር ደረጃ በደረጃ ተላቀው በነፃነት የሚሠሩበትን ስርዓት ለመዘርጋት ያለው ፋይዳ ከፍተኛ ስለመሆኑም ለኢዜአ ተናግረዋል፡፡

ተቋማዊ ነጻነት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተልዕኳቸውን  በተሻለ ሁኔታ ለማሳካት፣ የመምህራንን ሙያዊ አስተዋጾ ለማሳደግ እና ኑሯቸውን ለማሻሻል ትልቅ ሚና ያለው በመሆኑ መንግስት በትኩረት ይሠራበታል ነው ያሉት፡፡

ተቋማዊ ነጻነት ከመጪው 2015 ዓ.ም ጀምሮ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እንደሚተገበር ጠቁመው በሁለት ዓመታት ውስጥ 10 ዩኒቨርሲቲዎችን ራስ ገዝ ለማድረግ እየተሠራ ነው ብለዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.