Fana: At a Speed of Life!

በቻምፒየንስ ሊጉ ባየርሙኒክ እና ባርሴሎና በሞት ምድብ ተገናኝተዋል

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 19 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ የምድብ ድልድል በዛሬው እለት ይፋ ሆኗል።

ምሽት ላይ በተካሄደው ድልድል ምድብ ሶስት የሞት ምድብ ሆኗል።

ባየር ሙኒክ፣ ባርሴሎና፣ ኢንተር ሚላን እና ቪክቶሪያ ፕለዘን ያገናኘው ምድብ ታላላቅ ቡድኖችን እርስ በእርስ አገናኝቷል።

በሌሎች ምድቦች በምድብ አንድ አያክስ፣ ሊቨርፑል፣ ናፖሊ እና የስኮትላንዱ ሬንጀርስ ሲገናኙ፥ በምድብ ሁለት ደግሞ ፖርቶ፣ አትሌቲኮ ማድሪድ፣ ባየር ሌቨርኩዘን እና ክለብ ብሩጅ ተደልድለዋል።

በምድብ አራት ኤይንትራክት ፍራንክፈርት፣ ቶተንሃም ሆትስፐርስ፣ ስፖርቲንግ ሊዝበን እና ማርሴይ እንዲሁም የጣሊያኑ ሻምፒዮን ኤሲ ሚላን፣ ቼልሲ፣ ሳልዝበርግ እና ዳይናሞ ዛግሬቭ ደግሞ በምድብ አምስት ተገናኝተዋል።

በምድብ ስድስት የውድድሩ ባለ ክብረወሰን ሪያል ማድሪድ፣ ሌፕዚግ፣ ሻክታር ዶኔስክ እና የስኮትላንዱ ሻምፒዮን ሴልቲክ ሲደለደሉ፥ ማንቼስተር ሲቲ፣ ሴቪያ፣ ቦሩሲያ ዶርትመንድ እና ኮፐንሃገን የምድብ ሰባት ተፋላሚዎች ሆነዋል።

በመጨረሻው ምድብ ስምንት ደግሞ የፈረንሳዩ ሻምፒዮን ፒ ኤስ ጂ፣ ጁቬንቱስ፣ ቤኔፊካ እና የእስራኤሉ ማካቢ ሃይፋ ተደልድለዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.