Fana: At a Speed of Life!

“ማሜሎዲ ሳንዶውንስ”ን ለተቀላቀለው አቡበከር ናስር አቀባበል ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ አፍሪካውን ማሜሎዲ ሳንዶውንስ የተቀላቀለውን ኢትዮጵያዊ ፕሮፌሽናል የእግር ኳስ ተጫዋች አቡበከር ናስር በደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ዶክተር ሙክታር ከድር አቀባበል አደረጉለት፡፡

በአቀባበል ሥነ-ሥርዓቱ ላይ በደቡብ አፍሪካ የተባበሩት ኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ አመራሮችም እንደተገኙም ነው የተመለከተው፡፡

አምባሳደር ሙክታር ከድር ÷ በደቡብ አፍሪካ በሚኖረው ቆይታ ጠንከሮ በመስራት ወደ ላቀ የስኬት ማማ እንደሚደርስ ያላቸውን ተሥፋ ገልጸዋል፡፡

አቡበከር ናስር ለበርካታ የኢትዮጵያ ወጣቶችም ጠንክረው እንዲሰሩና ስኬታማ እንዲሆኑ ምሳሌ እንደሚሆንና በደቡብ አፍሪካና በሌሎችም ዓለምአቀፍ መድረኮች የኢትዮጵያን ሥም እንደሚያስጠራ እምነት አለኝ ብለዋል፡፡

የኤምባሲው እና በደቡብ አፍሪካ የሚገኙ ኢትየጵያዊያን ድጋፍ እንደማይለየውም አረጋግጠዋል።

አቡበከር ናስር በበኩሉ ÷ ለተደረገለት አቀባበል፣ ድጋፍ እና ማበረታቻ ምስጋና አቅርቦ ወደ ተሻለ ስኬት ለመሸጋገር ለሚያደርገው ጥረት ዐቅምና ሞራል እንደሚሆነው መናገሩን ከደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.