Fana: At a Speed of Life!

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ከ6 ሺህ 500 በላይ ተማሪዎችን እያስመረቀ ነው

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በተለያየ ሙያ እና መርሐ ግብር ያሰለጠናቸውን 6 ሺህ 515 ተማሪዎችን እያስመረቀ ነው፡፡

ዩኒቨርሲቲው በቅድመ ምረቃ፣ ሁለተኛ ዲግሪ፣ ሦስተኛ ዲግሪ እና በስፔሻሊቲ እንዲሁም በማሪታይም ሙያ ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች ነው ዛሬ እያስመረቀ የሚገኘው፡፡

ከተመራቂዎቹ መካከል፥ 3 ሺህ 910 በመጀመሪያ ዲግሪ፣ 1 ሺህ 597 በሁለተኛ ዲግሪ እና 69 በሦስተኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን የተከታተሉ መሆናቸው ተገልጿል፡፡

አል ቡሲራ ባሲኑር በኢትዮጵያ፣ በጂቡቲ እና በአፍሪካ ሕብረት የኢንዶኔዥያ አምባሳደር የዕለቱ የክብር እንግዳ በመሆን በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ ተገኝተዋል፡፡

በተመሳሳይ መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛና ተከታታይ መርሐ ግብር ያሰለጠናቸውን 253 የ3ኛ ዙር ተመራቂ ተማሪዎችን አስመርቋል፡፡

በታሪኩ ለገሰ፣ በሳራ መኮንን እና በግርማ ነሲቡ

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.