Fana: At a Speed of Life!

ሁሉም ትግረዋይ ወደ ጦርነት የገባው ህወሓት ወደ ሰላም ውይይት እንዲመለስ በሕብረት ጫና ሊፈጥር ይገባል – የመከላከያ ሚኒስትሩ 

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)  በየትኛውም አካባቢ የሚገኝ ትግረዋይ ወደ ጦርነት የገባው የህወሓት ቡድን ወደ ሰላም ውይይት እንዲመለስ ከማናኛውም ግዜ በላይ በሕብረት ጫና እንዲፈጥር የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስትር አብረሃም በላይ ጥሪ አቀረቡ።

ሚኒስትሩ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ባወጡት መልዕክት፥ የሰላም እና የውይይት መንገድን እምቢ ብሎ ጦርነት በመጀመር የሚመጣ ጥቅምም ሆነ የሚመለስ የህዝብ ጥያቄ የለም ብለዋል።

በዚህ ጊዜ የትግራይ ህዝብ የሚፈልገው ነገር ግን ያጣው ነገር ቢኖር ለሰላምና ውይይት ቅድሚያ የሚሰጥ መሪ ነው ያሉት ሚኒስትሩ፥ አሁንም ለሰላም አማራጭ አልረፈደም ብለዋል።

“በተለይ ከትግራይ ውጪ የሚገኝ የትግራይ ተወለጀ እና የትግራይ ህዝብ ወዳጅ፥ ህዝባችንን ወደ ጦርነት እየመራ ያለዉን ቡድን እንዲያቆም እና ወደ ሰላም ውይይት እንዲመለስ ከማናኛውም ጊዜ በላይ በሕብረት ጫና መፍጠር ይገባዋል” ነው ያሉት በመልዕክታቸው።

“በትግራይ ተወላጆች መካካል የፖለቲካ ልዩነት መኖሩ ተፈጥሯዊ ነው፤  ነገር ግን ለህዝባችን ሞት፣ እስካሁን የከፈለው መስዋእትነት እና ችግር ይበቃዋል” ብለዋል።

የትግራይ ህዝብ ጉዳይ የሁሉ ጉዳይ መሆኑን በማንሳት፥ የሆነ ቡድን ወይም ሀይል ብቻ በሚሰጠው  አማራጭ ብቻ መፍሰስ ትክክል አለመሆኑን ጠቁመዋል።

ህዝቡ ሊጠይቅ፣ አማራጭ እና የመፍትሄ ሃሳቦችን ይዞ ሊቀርብ ይገባል ነው ያሉት።

የትግራይ ህዝብ ተጨማሪ ጦርነት አይገባውም ያሉት ሚኒስትር አብረሃም በላይ፥ “የህዝባችን ችግርና ጉስቁልና እንዲያበቃ በተለይ የተማረው የትግራይ ተወላጀ ሚዛናዊ ሆኖ የበኩሉን አስተዋፅኦ እንደዲያረግ ጥሪ አቅርበዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.