Fana: At a Speed of Life!

የአውሮፓ ኅብረት ሩሲያ ላይ የጣለው ማዕቀብ ውጤት አላመጣም ተባለ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 21 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ምዕራባውያኑ ሩሲያ ላይ የጣሉት ማዕቀብ የተፈለገውን ውጤት አላስገኘም ተባለ፡፡

የአውሮፓ ኅብረት ማዕቀቡን ሲጥል የሚሻውን ውጤት በስትራቴጂ ደረጃ በግልፅ እንዳላስቀመጠ እና ችግሮች እንዳሉበት ዘ ኢኮኖሚስት ማስነበቡን አር ቲ ዘግቧል፡፡

ምንም እንኳን ሩሲያ ማዕቀቡ በተጣለባት ሰሞን የኢኮኖሚ መንገጫገጭ ቢያጋጥማትም አሁን ላይ ግን የፋይናንስ ሥርዓቷ መረጋጋቱን ዘገባው አመላክቷል።

አሁን ላይ ሩሲያ ቻይናን ጨምሮ አንዳንድ የወጪ ንግድ ምርቷን የሚቀበሉ አዳዲስ አስመጪዎችን ማግኘት መቻሏም ተጠቁሟል፡፡

በማዕቀቡ ምክንያት የተከሰተው የኃይል አቅርቦት እጥረት በአውሮፓ የዋጋ ግሽበት ሊያስከትል ይችላልም ነው የተባለው።

በአውሮፓ በዚህ ሣምንት የጋዝ ዋጋ በ20 በመቶ መጨመሩን አንድ የብሪታኒያ ጋዜጣ ማስነበቡም ተጠቁሟል፡፡

የ1990ዎቹ የአሜሪካ የበላይነት ካበቃለት መቆየቱንና የምዕራቡ ዓለም ሀገራትም በኢራቅ እና በአፍጋኒስታን ከተደረጉ ጦርነቶች በኋላ ወታደራዊ ኃይል የመጠቀም ፍላጎታቸው እየቀነሰ መምጣቱንም ዘ ኢኮኖሚስት በዘገባው አመላክቷል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.