Fana: At a Speed of Life!

ለአሸባሪው የሕወሓት ቡድን ሊደርስ የነበረ ነዳጅ በአፋር ክልል ኢረብቲ ተያዘ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰላም መንገድን አሻፈረኝ በማለት ዳግም ጥቃት የከፈተው የሕወሓት ሽብር ቡድን ለወረራ ግብአት ለማድረግ ሲያጓጉዘው የነበረ ነዳጅ በአፋር ክልል ኢረብቲ ላይ ተይዟል።
የአፋር ክልል የጸጥታ ሃይል በተለይ የኢረብቲ የጸጥታ መዋቅር በቁጥጥር ስር ያዋለው ነዳጅ የሽብር ቡድኑ በቀጣይ ለወረራ ሊጠቀምበት እንደነበርም ታውቋል።
ከቀናት በፊት ለሰብአዊ እርዳታ መቀሌ የነበረን ነዳጅ የሽብር ቡድኑ መዝረፉን የዓለም ምግብ ድርጅት ማስታወቁ ይታወሳል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.