Fana: At a Speed of Life!

ኢንዱስትሪ ፓርኩ የሀገር መከላከያ ሰራዊትና የኦሮሚያ ልዩ ሀይል ዩኒፎርሞችን ማምረት ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሀገር መከላከያ ሰራዊት እና የኦሮሚያ ክልል ልዩ ሀይል ወታደራዊ ዩኒፎርም (መለዮ) በሀዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ መመረት መጀመራቸውን የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን አስታወቀ፡፡

የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሳንዶካን ደበበ፣ የኮርፖሬሽኑ የትራንስፎርሜሽንና ዋና ስራ አስፈፃሚ ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ፍፁም ከተማ እንዲሁም ሌሎች የስራ ሀላፊዎች የሀዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክን ጎብኝተዋል፡፡

በጉብኝታቸው “ኢፒክ አፓረል “የተሰኘውንና የሀገር መከላከያ ሰራዊት ዩኒፎርምን እንዲሁም የኦሮሚያ ክልል ልዩ ሀይል ዩኒፎርሞችን የሚያመርት ኩባንያን የስራ እንቅስቃሴ ተመልክተዋል፡፡

በሀዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ የሚገኘው ኩባንያው ዩኒፎርሞቹን ከሁለት ሳምንት በፊት ማምረት የጀመረ ሲሆን፥ በምርት ሂደቱ ላይ ባሉ እንቅስቃሴዎች ዙሪያ ከኮርፖሬሽኑ ከፍተኛ ሀላፊዎች ጋር ውይይት ተካሂዷል፡፡

ከ177 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር በላይ በሆነ ወጪ ስራውን የጀመረው ኩባንያው አሁን ላይ የጨርቃ ጨርቅ ዘርፉ ላይ በመሰማራት ከ2 ሺህ 500 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ እድል ፈጥሯል፡፡

ሀዋሳ ኢንዱስተሪ ፓርክ ደግሞ በአሁን ሰዓት ከ20 በላይ አምራች ኩባንያዎችን በውስጡ የያዘ ሲሆን፥ በኢትዮጵያ ካሉ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ቀደምት ከሚባሉት የሚጠቀስ መሆኑን ከኮርፖሬሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.