Fana: At a Speed of Life!

የቡና ምርትና ጥራትን ለማሳደግ ለአርሶ አደሩ የሚደረገው እገዛ ይጠናከራል – አቶ ደስታ ሌዳሞ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የቡና ምርት እና ጥራትን ለማሳደግ ለአርሶ አደሩ የሚደረገው ሙያዊ እገዛ እንደሚጠናከር የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ ተናገሩ፡፡

የሲዳማ ክልል የእርሻና ተፈጥሮ ሃብት ቢሮ የቡና፣ ፍራፍሬና ቅመማቅመም ልማት ንቅናቄ መድረክ በሐዋሳ ከተማ እያካሄደ ነው፡፡

ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ በክልሉ የቡና ምርት በከፍተኛ መነቃቃት ትኩረት ተሰጥቶ መሠራቱን ጠቁመው÷ በጥራትም ከፊት መሰለፉን አብራርተዋል፡፡

የቡና ምርትን ለማስፋትና ጥራት ለመጨመር በግብርና ባለሙያ ለአርሶ አደሩ እየተደረገ ያለው እገዛ እንደሚጠናከር እና አርሶ አደሮችም የባለሙያዎችን አቅጣጫ እንዲከተሉ አሳስበዋል።

አቶ ደስታ የፍራፍሬ ምርታማነትን በማሳደግ አርሶአደሩን ተጠቃሚ ለማድረግ ይሠራል ማለታቸውን የርዕሰ መስተዳድር ጽህፈት ቤት መረጃ ያመለክታል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.